Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 1:53

[1] ለጣዖታት ስለሚሠዉ መሥዋዕቶች ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን፤ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።

[2] ዐወቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያውቅ የሚገባውን ገና አላወቀም።

[3] እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ግን እርሱ በእርሱ ዘንድ በእውነት የታወቀ ነው።

[4] ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

[5] አማልክት የሚሉአቸው ነገሮች አሉና፤ በሰማይም ቢሆን፥ በምድርም ቢሆን፥ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥

[6] ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።

[7] ነገር ግን ሁሉ የሚያውቀው አይደለም፤ እስከ ዛሬ በጣዖታት ልማድ፥ ለጣዖት የተሠዋውን የሚበሉ አሉ፤ ኅሊናቸውም ደካማ ስለሆነ ይረክሳል።

[8] መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ ባንበላም አይጎዳንም።

[9] ነገር ግን እናንተን በማየት ሌላው እንዳይሰናከል ተጠንቀቁ።

[10] አንተ አማኙ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲያው ለጣዖት የተሠዋውን ደፍሮ ይበላል።

[11] ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለት ያ ደካማ ወንድም አንተን በማየት ይጎዳል።

[12] በባልንጀሮቻችሁ ላይ እንዲህ የምትበድሉ ከሆነ ደካማ ሕሊናቸውንም የምታቈስሉ ከሆነ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

[13] ነገር ግን በመብል ምክንያት ወንድሜ የሚሰናከል ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክል ለዘለዓለም ሥጋን አልበላም።

ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 — Chapters