Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 6:03

[1] ፍቅርን ተከተሏት፤ ለመንፈሳዊ ስጦታ፥ ይልቁንም ትንቢት ለመናገር ተፎካከሩ።

[2] በቌንቌ የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው የሚናገር አይደለም። የሚናገረውን የሚሰማው የለምና፥ ነገር ግን በመንፈስ ምሥጢርን ይናገራል።

[3] ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር፥ ለማረጋጋትም ለሰው ይናገራል።

[4] በቌንቌ የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ የሚተረጕuም ግን የክርስቲያን ማኅበርን ያንጻል።

[5] ሁላችሁም በቌንቌ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕuም በቌንቌ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕuም ግን ማኅበሩን ያንጻል።

[6] አሁንም ወንድሞቼ ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቌንቌ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው?

[7] ነፍስ የሌለው ድምፅ የሚሰጥ እንደ መሰንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣሪያ በስልት ካልተመታ መሰንቆው ወይም ክራሩ የሚለውን ማን ያውቃል?

[8] መለከት የሚነፋም በታወቀው ስልት ካልነፋ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?

[9] እንዲሁም እናንተ በማይታወቅ ቌንቌ ብትናገሩ፥ ይህንኑም ገልጣችሁ ባትተረጕuሙ የምትሉትንና የምትናገሩትን ማን ያውቃል? ከነፋስ ጋር እንደምትነጋገሩ ትሆናላችሁ።

[10] በዓለም ልዩ ልዩ ቌንቌዎች አሉ፤ ከእነርሱም ትርጕuም የሌለው አንድም የለም።

[11] የቌንቌውን ትርጓሜ ካላወቅሁ እኔ ለሚያነጋግረኝ እንደ እንግዳ እሆንበታለሁ፤ የሚያነጋግረኝ እርሱም ለእኔ እንደ እንግዳ ይሆናል።

[12] እንዲሁ እናንተም ለመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተፎካከሩ፤ ትበዙም ዘንድ ማኅበሩ የሚታነጽበትን ፈልጉ።

[13] በማያውቀው ቌንቌ የሚናገር ሰውም መተርጐም እንዲችል ይጸልይ።

[14] በማላውቀው ቌንቌ የምጸልይ ከሆንሁ ቃሌ ብቻ ይጸልያል፤ ልቤ ግን ባዶ ነው።

[15] እንግዲህ ምን አደርጋለሁ በመንፈስ እጸልያለሁ፤ በማስተዋልም እማልዳለሁ፤ በመንፈሴ እዘምራለሁ፤ በማስተዋልም እዘምራለሁ።

[16] አንተ በመንፈስ ብታመሰግን፥ ያ የቆመው ያልተማረው በአንተ ምስጋና ላይ እንዴት አሜን ይላል? የምትናገረውንና የምትጸልየውን አያውቅምና።

[17] እነሆ፥ አንተስ መልካም ታመሰግናለህ፤ ነገር ግን ሌላው እንዴት ይታነጻል?

[18] እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ከሁላችሁ ይልቅ እኔ በቌንቌዎች እናገራለሁና።

[19] ነገር ግን ሌሎችን አስተምር ዘንድ፥ በቌንቌ ከሚነገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክርስቲያን በአእምሮዬ አምስት ቃላትን ልናገር እሻለሁ።

[20] ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።

[21] በኦሪትም ፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቌንቌዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር ” ብሎአል።

[22] አሁንም ቌንቌ መናገር ለማያምኑ ሰዎች ለምልክት ነው፤ ለሚያምኑ ግን አይደለም፤ ትንቢትም ለሚያምኑ ነው እንጂ ለማያምኑ አይደለም።

[23] ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቌንቌ ቢናገሩ፥ አላዋቂዎች፥ ወይም የማያምኑ ቢመጡ አብደዋል ይሉአቸው የለምን?

[24] ሁሉም ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምኑ ወይም አላዋቂዎች ቢመጡ ሁሉ ይከራከሩአቸው የለምን? ሁሉስ ያሳፍሩአቸው የለምን?

[25] በልባቸው የደበቁትም ይገለጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማያምነው ተመልሶ ይጸጸታል፤ በግንባሩም ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፥ በእውነት እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለም ይናገራል።

[26] አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሁላችሁ በምትሰበሰቡበት ጊዜ መዝሙር አላችሁ፤ ትምህርት አላችሁ፤ መግለጥ አላችሁ፤ በቌንቌ መናገር አላችሁ፤ መተርጐምም አላችሁ፤ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት።

[27] በቌንቌ የሚናገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየሆኑ በተራ ይናገሩ፤ ሌላውም ይተርጕuምለት።

[28] የሚተረጕuም ከሌለ ግን በቤተ ክርስቲያን በቌንቌ የሚናገረው ዝም ይበል፤ በእግዚአብሔር መካከልና በእርሱ መካከል ይናገር።

[29] ነቢያትም ቃላቸው ለቤተ ክርስቲያን ይታወቅ ዘንድ ሁለት ሁለት፥ ወይም ሦስት ሦስት ሆነው ይናገሩ።

[30] ተቀምጦ ሳለ ምሥጢር የተገለጠለት ቢኖር ፊተኛው ዝም ይበል።

[31] ሁሉ እንዲማር፥ ሁሉም ደስ እንዲለው፥ እንዲጸናም ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁና።

[32] የነቢያት ሀብት ለነቢያት ይሰጣልና።

[33] በቅዱሳን ጉባኤ ሁሉ እንደሚደረግ፥ እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና።

[34] ሴቶችም በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሊታዘዙ እንጂ ሊናገሩ አልተፈቀደምና፤ ኦሪትም እንዲህ ብሎአልና።

[35] ለሴት በቤተ ክርስቲያን መናገር ክልክል ነው፤ ሊማሩ ከወደዱ ደግሞ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።

[36] የእግዚአብሔር ቃል ከእናንተ ብቻ ወጥቶአልን? ወይስ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እናንተ ብቻ ደርሶአልን?

[37] ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት አድርጎ የሚቈጥር ቢኖር፥ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ይህን የጻፍሁላችሁን ይወቅ።

[38] ነገር ግን ይህን የማያውቅ ቢኖር እግዚአብሔርን አያውቀውም።

[39] አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ትንቢትን ለመናገር ቅኑ፤ በቌንቌ የሚናገረውንም አትከልክሉት።

[40] ነገር ግን ሁሉን በአገባብና በሥርዐት አድርጉ፤

ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 — Chapters