Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 4:35

[1] ወንድሞቻችን ሆይ፥ አባቶቻችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረዳቸው ሁሉም በባሕር መካከል አልፈው እንደ ሄዱ ልታውቁ እወዳለሁ።

[2] ሁሉንም ሙሴ በደመናና በባሕር አጠመቃቸው።

[3] ሁሉም ያን መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ።

[4] ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸውም በኋላቸው ከሚሄደው ከመንፈሳዊ ዐለት የጠጡት ነው፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።

[5] እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሁሉም ደስ አላለውም፤ ብዙዎቹ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።

[6] እነርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እንዳንመኝ እነርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑልን።

[7] “አሕዛብ ተቀመጡ፤ ይበሉና ይጠጡም ጀመር፤ ሊዘፍኑም ተነሡ ” ብሎ መጽሐፍ እንደ ተናገረ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንደ አመለኩ ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።

[8] ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አንሴስን።

[9] ከእነርሱም አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንደ ተፈታተኑት፥ ነዘር እባብም እንደ አጠፋቸው እግዚአብሔርን አንፈታተን።

[10] ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጐራጐሩበት፥ በመቅሠፍትም እንደጠፉ አናንጐራጕuር።

[11] እነርሱን ያገኛቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለምንነሣው ለእኛ ትምህርትና ምክር ሊሆነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።

[12] አሁንም ያ ቆሜአለሁ ብሎ በራሱ የሚታመን ሰው እርሱ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።

[13] በሰው ላይ እንደሚደርሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያገኛችሁም። በምትችሉት መከራ ነው እንጂ በማትችሉት መከራ ትፈተኑ ዘንድ ያልተዋችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፤ እርሱም ከፈተና ትድኑ ዘንድ በመከራ ጊዜ ይረዳችኋል።

[14] ወንድሞቼ! አሁንም ጣዖት ከማምለክ ሽሹ።

[15] ለዐዋቂዎች እንደሚነገር እነግራችኋለሁ፤ ትክክለኛውንም እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።

[16] ይህ የምንባርከው የበረከት ጿ ከክርስቶስ ደም ጋር አንድ አይደለምን? የምንፈትተው ይህስ ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይደለምን?

[17] ኅብስቱ አንድ እንደ ሆነ እንዲሁ እኛም ብዙዎች ስንሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላችን ከአንድ ኅብስት እንቀበላለንና።

[18] እስራኤል ዘሥጋን ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን ይበላሉ፤ ከመሠዊያውም ጋር አንድ ይሆኑ አልነበረምን?

[19] እንግዲህ ምን እንላለን? ለጣዖታት የሚሠዋ መሥዋዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖቶቻቸውም ከንቱ ናቸው።

[20] አሕዛብም የሚሠዉ ለአጋንንት ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም፤ ነገር ግን የአጋንንት ተባባሪዎች እንድትሆኑ አልፈቅድላችሁም።

[21] የእግዚአብሔርን ጿና የአጋንንትን ጿ አንድ አድርጋችሁ መጠጣት አትችሉም፤ የእግዚአብሔርን ማዕድና የአጋንንትንም ማዕድ በአንድነት ልትበሉ አትችሉም።

[22] እንግዲህ እግዚአብሔርን እናስቀናውን? በውኑ እኛ ከእርሱ እንበረታለን?

[23] ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።

[24] ለባልንጀራችሁ እንጂ ለራሳችሁ አታድሉ።

[25] ደግሞም በሥጋ ገበያ የሚሸጡትን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ።

[26] “ምድር በመላዋ የእግዚአብሔር ናትና።”

[27] ያላመነ ሰው ቢጠራችሁ፥ ልትሄዱም ብትወዱ ያቀረቡላችሁን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ።

[28] እንግዲህ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው ” ያላችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገራችሁና ባልንጀራችሁም የሚጠራጠር ስለሆነ አትብሉ።

[29] ነጻነታችሁን እንዳይነቅፉአት አስረድተዋችኋልና።

[30] በጸጋ ብበላ ግን በነገሩ ስለማመሰግን ለምን ይነቅፉኛል።

[31] ብትበሉም፥ ብትጠጡም የምታደርጉትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

[32] ለአይሁድም፥ ለአረማውያንም፥ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ያለ ማሰናከል አርአያ ሁኑአቸው።

[33] እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እንዳሰኝ ይድኑ ዘንድ የብዙዎችን ተድላ እሻለሁ እንጂ የራሴን ተድላ የምሻ አይደለሁምና።

ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 — Chapters