[1] ስለዚህም የክርስቶስን የነገሩን መጀመሪያ ትተን ወደ ፍጻሜው እንሂድ፤ እንግዲህ ደግሞ ሌላ መሠረት እንዳትሹ ዕወቁ፤ ይኸውም ከሞት ሥራ ለመመለስ፥ በእግዚአብሔርም ለማመን፥
[2] ጥምቀትን፥ በአንብሮተ እድ መሾምን፥ የሙታንን ትንሣኤና የዘለዓለም ፍርድን ለመማር ነው።
[3] እግዚአብሔርም ቢፈቅድ ይህን ባደረግን ነበር።
[4] ነገር ግን አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን፥ ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን፥ ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን፥
[5] መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል፥ የሚመጣውንም የዓለምን ኀይል የቀመሱትን፥
[6] በኋላም የካዱትን እንደ ገና ለንስሓ እነርሱን ማደስ አይቻልም፤ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና፥ ያዋርዱትማልና።
[7] ምድርም በእርስዋ የሚወርደውን ዝናም ከጠጣች፥ ያንጊዜ ስለ እርሱ ያረሱላትን መላካም ቡቃያ ታበቅላለች፤ ከእግዚአብሔር ዘንድም በረከትን ታገኛለች።
[8] እሾህንና ኵuርንችትን ብታወጣ ግን የተጣለች ናት፤ ለመርገምም የቀረበች ናት፤ ፍጻሜዋም ለመቃጠል ይሆናል።
[9] የተመረጣችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምንም እንኳን እንዲህ ብንላችሁ ሕይወት ወዳለባት ትምህርት እንድትቀርቡ እንታመንባችኋለን።
[10] እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስለ አገለገላችሁ፥ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችትሁን ሥራ፥ በስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።
[11] ነገር ግን ሁላችሁም በዚች ተስፋችሁ እንዲሁ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻው ታሳዩ ዘንድ እንወዳለን።
[12] ዳተኟች እንዳትሆኑ በሃይማኖትና በትዕግሥት ተስፋቸውን የወረሱትን ሰዎች ምሰሉአቸው።
[13] እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋዉን በሰጠው ጊዜ ይምልበት ዘንድ ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ ባይኖር፥ በራሱ ማለ።
[14] እንዲህ ብሎ ፥ “ መባረክን እባርክሃለሁ፥ ማብዛትንም አበዛሃለሁ።”
[15] ከዚህም በኋላ ታግሦ ተስፋዉን አገኘ።
[16] ሰው ግን ከእርሱ በሚበልጠው ይምላል፤ የክርክርም መነሻው በመሐላ ይፈጸማል።
[17] ስለዚህም እግዚአብሔር ተስፋውን ለሚወርሱ ሰዎች ምክሩን እንደማይለውጥ ሊገልጥ ወደደ፤ እንደማይለውጥም በመሓላ አጸናው።
[18] የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።
[19] ይህችም ተስፋ ነፍሳችን እንዳትነዋወጥ እንደ መልሕቅ የምታጸና ናት፤
[20] እንደ መልከ ጽዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ሊቀ ካህናት ሆኖ ሐዋርያችን ኢየሱስ ከእኛ በፊት ወደ ገባባት መጋረጃም ውስጥ የምታስገባ ናት።