Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:47

[1] አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ በእኛ ዘንድ እንደ ታዘዛችሁ በሚገባ ትሄዱ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ደስ ታሰኙ ዘንድ፥ ደግሞ እንደ ሄዳችሁ ከፊት ይልቅ በዚሁ ታበዙና ትጨምሩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንነግራችኋለን፤ እንማልዳችኋለንም።

[2] በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም ያዘዝናችሁን ትእዛዝ ታውቃላችሁ።

[3] የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነውና፤ እርሱም ከዝሙት ትርቁ ዘንድ መቀደሳችሁ ነው።

[4] ሁሉም እያንዳንዱ ገንዘቡን ይወቅ፤ በንጽሕናና በክብርም ይጠብቀው።

[5] እግዚአብሔርን እንደማያውቁት እንደ አረማውያንም በፍትወት ድል አትነሡ።

[6] ይህንም ለማድረግ አትደፋፈሩ፤ በሁሉም ወንድሞቻችሁን አትበድሉ፤ አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁና እንደ አዳኘሁባችሁ፥ በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር የሚበቀል ነውና።

[7] እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኵuሰት አልጠራንምና።

[8] አሁንም የሚክድ፥ መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን የካደ አይደለም።

[9] ባልንጀሮቻችሁን ስለ መውደድ ግን ልንጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ እርስ በርሳችሁ እንድቷደዱ ራሳችሁ በእግዚአብሔር የተማራችሁ ናችሁና።

[10] በመቄዶንያ ሁሉ ካሉት ወንድሞቻችን ሁሉ ጋር እንዲሁ ታደርጋላችሁ፤ ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ፥ ትበዙና ትጨምሩ ዘንድ እንማልዳችኋለን።

[11] የዋሃንም ትሆኑ ዘንድ፥ ሥራችሁንም ታከናውኑ ዘንድ እንደ አዘዝናችሁም በእጃችሁ ትሠሩ ዘንድ፥

[12] በውጭ ባሉት ሰዎችም ዘንድ ከማንም አንዳች ሳትሹ በሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናችኋለን።

[13] ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስለ ሞቱ ሰዎች፥ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን።

[14] ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል፤ ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል።

[15] ይህንም በእግዚአብሔር ቃል እንነግራችኋለን፤ ጌታችን በሚመጣ ጊዜ ሕያዋን ሆነን የምንቀር እኛ የሞቱትን አንቀድማቸውም።

[16] ጌታችን ራሱ በትእዛዝ፥ በመላእክትም አለቃ ድምፅ፥ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ በክርስቶስም የሞቱ ሙታን አስቀድመው ይነሣሉ።

[17] ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታችንን በአየር እንቀበለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። ከዚያም ወዲያ ለዘለዓለሙ ከጌታችን ጋር እንኖራለን።

[18] ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1 — Chapters