[1] የእግዚአብሔር አብና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ከሚሆን ከያዕቆብ፥ ለተበተኑ ዐሥራ ሁለቱ ነገድ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
[2] ወንድሞች ሆይ፥ ልዩ ልዩ መከራ በሚመጣባችሁ ጊዜ በሁሉ ደስ ይበላችሁ።
[3] በሃይማኖታችሁ የሚመጣው ፈተና ትዕግሥትን እንደሚያደርግላችሁ ዐውቃችሁ፥
[4] ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ጤነኟች ትሆኑ ዘንድ ትዕግሥት ፍጹም ግብር አላት።
[5] ጥበብን ያጣት ሰው ቢኖር፥ ሳይነቅፍና ሳይነፍግ ለሁሉ በልግስና የሚሰጥ እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።
[6] ነገር ግን አምኖ ይለምን፤ አይጠራጠርም፤ የሚጠራጠር በነፋስ የሚገፋና የሚነዋወጥ የባሕር ማዕበልን ይመስላልና።
[7] ለዚያ ሰው ከእግዚአብሔር ምንም የሚያገኝ አይምሰለው።
[8] ሁለት ልብ የሆነ ሰው በመንገዱ ሁሉ ይታወካልና።
[9] ድሃው ወንድማችን ከፍ ከፍ በማለቱ ይመካ።
[10] ባለጠጋውም በመዋረዱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
[11] ፀሐይ ከሙቀቱ ጋር በወጣ ጊዜ ሣሩን ያደርቀዋል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የመልኩም ውበት ይጠፋል፤ እንዲሁ ባለጠጋም በመንገዱ ይዝላል።
[12] መከራን የሚታገሥ ሰው ብፁዕ ነው፤ ተፈትኖ እግዚአብሔር ለሚወዱት ተስፋ ያደረገላቸውን የሕይወት አክሊል ይቀበላልና።
[13] የሚፈተን ሰው ቢኖር እግዚአብሔር ይፈትነኛል አይበል፤ እግዚአብሔር ለክፉ ነገር አይፈትንምና፤ እርሱስ ማንንም አይፈትንም።
[14] ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኟት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
[15] ምኟትም ከፀነሰች ኀጢአትን ትወልዳታለች፤ ኀጢአትም ከተፈጸመች ሞትን ትወልዳታለች።
[16] የተወደዳችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ አትሳቱ።
[17] መልካም ሀብት ሁሉ፥ ፍጹም ዕድልም ሁሉ ከላይ ነው፤ ከብርሃናት አባት ዘንድ ይወርዳል፤ እርሱም መለወጥ የሌለበት ነው፤ ከእጁም የሚያመልጥ ምንም የለም።
[18] ለፍጥረቱ ተቀዳሚዎች እንሆን ዘንድ በፈቃዱ በእውነት ቃሉ ወለደን።
[19] አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርም የዘገየ፥ ለቅWጣም የዘገየ ይሁን።
[20] የሰው ቅWጣው የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያሠራውምና።
[21] አሁንም ርኵuሰትን ሁላ፥ ክፋትንም ሁላ አስወግዷት፤ ነፍሳችሁንም ማዳን የሚችለውን፥ በልባችሁ የተዘራውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉት።
[22] ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ፥ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
[23] ቃሉን ሰምቶ የማያደርገው ቢኖር፥ የተፈጥሮ ፊቱን በመስታዋት እንደሚያይ ሰው ይመስላል።
[24] ራሱንም ተረድቶ ይሄዳል፤ ወዲያውም እንዴት እንደ ሆነ ይረሳል።
[25] ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ የሚመለከትና የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ የሰማውን የሚዘነጋ ያይደለ ይህ በሥራው ብፁዕ ነው።
[26] አንደበቱን ሳይገታ፥ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር፥ የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው።
[27] ንጹሕ የሆነ፥ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች፥ ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ ርኵuሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው።