"የሐበሻ ማኅበረሰብ መጥቶ ቢያየኝ፤ ቢደግፈኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነገር የሚያገኝበት ትዕይንት ነው" ሶሊያና እርሴ
23 April 2026

"የሐበሻ ማኅበረሰብ መጥቶ ቢያየኝ፤ ቢደግፈኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነገር የሚያገኝበት ትዕይንት ነው" ሶሊያና እርሴ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

About
ሶሊያና እርሴ፤ ትንፋሽ አስዋጭ፣ የልብ ትርታን ደላቂ፣ ከዮጋም፣ ከጂምናስቲክም ልዩ አካላዊ እጥፋትና ዝርጋታን፣ ልዩ ምትሃት መሰል ክህሎትን ግድ የሚለው፤ ግና ሞገስን ተላብሶ መድረክ ላይ ግዘፍ የሚነሳ Contortionist Extraordinaire ኢትዮጵያዊት ናት። ድንቅ ክህሎቷም ከኤፕሪል 7 እስከ ሜይ 24 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከClub Kabarett ጋር ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎቿ እንዲሆኑ ትጋብዛለች።