04 October 2026
አዲስ የሚመሰረተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት ቀዉስ ሊያወጣ የሚችል መፍትሄን ያገኝ ይሆን?
እንወያይ | Deutsche Welle
About
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ፤ አዲስ መንግሥት የሚመሰርተዉ፤ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዲስ ጦርነት ተቀሰቀሰ ከተባለ በኃላ ነዉ። ጦርነቱ የጀመረዉ በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት፤ የአማራ ፋኖ፤ የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ሰራዊትን ጨምሮ 7 አማፂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የጋራ ጥምረት በመሰረቱ በሁለተኛዉ ቀን መሆኑ ነዉ።