
About
በዜና መጽሔት ዝግጅታችን አዲስ አበባ ውስጥ የተሰየመው የትግራይ ምክክር እና አንድምታው፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዲሱ “የህገወጥ ቤቶች ግንባታ” ደንብ እና ያስተናገደው አስተያየት ፤ገቢና ወጪ ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሥራቸው በምን ኹኔታ ላይ ይገኛል? የሚለውን ጨምሮ ፤ በነዳጅ እጥረት ቀውስ በሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖን የተመለከቱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው ።