የጥር 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና
03 February 2026

የጥር 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከመንግሥታቸው ወግኖ የተዋጋው የኤርትራ ጦር በአክሱም ከተማ “ወጣቶች በጅምላ” እንደረሸነ ለመጀመሪያ ጊዜ አመኑ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባሕር ዳር ከተማ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኜ ገዳይ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ። የሱዳን ጦር በመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና አጋሮቹ በካዱግሊ ከተማ ላይ ያደረጉትን ከበባ ሰበረ። ሩሲያ ለሊቱን በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንደፈጸመች ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ።