የታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
01 January 2026

የታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
የታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አንደኛ የፀረ-ሽብርና ሕገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ ከቀረቡት ሶስት የክስ ጭብጦች አንደኛው እንዲሻሻል ዛሬ በየነ። የተጠየቀው የዋስትና መብት ውድቅ እንዲሆንም ወስኗል።

በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ህዝቡ አዲሱን ጎርጎሮሳዊውን 2026 ዓ.ም. በፌሽታና በቀለማት ያሸበረቁ ርችቶችን በማፈንዳት ተቀብሏል።

ስዊስ አልፓይን በሚገኝ አንድ ቡና ቤት ውስጥ በተካሄደ የአዲስ ዓመት አከባበር ላይ በተነሳ እሳት በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ አስግቷል።