የታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
10 December 2025

የታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ የ13 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው።
በዓለም የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ እየቀነሰ፤ ፀረ መብት ለሆኑ እንቅስቃሴዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ እየጨመረ መሆኑን የተመድ አመለከተ።
ሩዋንዳ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ቡሩንዲ ሆን ብለው የሰላም ስምምነቱን እየጣሱ ነው ስትል ከሰሰች። ዴሞክራቲክ ኮንጎ በበኩላ ዩናይትድ ስቴትስ ሩዋንዳን አደብ ታስገዛልኝ ብላለች።
ሩሲያ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከምዕራብ ሃገራት መሪዎች ብቸኛው የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የሚገዳቸው መሪ ናቸው አለች።