የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
12 March 2026

የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
ዐርእስተ ዜና

አሜሪካን የጠረዘቻቸው 4 ተጨማሪ ሰዎች ኤስዋቲኒ ተቀበለች ተጠራዦች ሁለቱ ከሶማሊያ አንድ ከታንዛኒያ ሌላ አንድ ደግሞ ከሱዳን መሆናቸው ተገልጿል።

አዲሱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻማኒ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መዘጋት እንደ ማነቃቂያ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ተናገሩ፤ ኢራን ጎረቤቶቿን የባህረ ሰላጤው አገራትን ማጥቃቷን እንደምትቀጥልም አስታወቁ

ቱርክና ጀርመን የኢራን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ተስማሙ። ጀርመን አውሮጳውያንና የባህረ ሰላጤው አገራት የኢራንን ጦርነት ለማስቆም በጋራ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበች።