Skip to content
Opens in a new window
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ  11 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
17 August 2026

የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ

የዓለም ዜና

About
አርስተ ዜና
--የሞሮኮ የጸጥታ ኃይሎች ድንበር አቋርጠዉ የስፔን ራስ-ገዝ ወደ ሆነችዉ ሴዑታ በየብስ እና በባህር አቋርጠዉ ለመግባት የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በቁጥጥር አዋሉ።-የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ኅልውና፣ ባለቤትነት እና የራስ-አስተዳደር መብት ዙሪያ "የክህደት ተግባር" ታይቷል ሲል እርምት ጠየቀ። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ባወጣዉ መግለጫ፤ የአብንን "ድምዳሜ የማይጋራው መሆኑን" ገልጿል።-የኢራን ጦር አንድ የአሜሪካ ወታደርን ለያዘ ወይም ለገደለ ሰው 30,000 ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታወቀ።