የዓለም ዜና ፤ መጋቢት 1 ቀን 2018 ማክሰኞ
10 March 2026

የዓለም ዜና ፤ መጋቢት 1 ቀን 2018 ማክሰኞ

የዓለም ዜና

About
አርስተ ዜና፤-የኢራን ሲቪሎች ከአሜሪካና ከእስራኤል የአየር ጥቃቶችና በኢንተርኔት መቆራረጥ ያለምንም ከለላ አጣብቂኝ ዉስጥ ናቸዉ። የአገዛዙ ተቃዋሚዎችም ጦርነቱ በቅርቡ ያበቃል የሚል ተስፋ እያጡ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ጦርነቱ በቅርቡ ያበቃል ማለታቸዉን ተከትሎ የዓለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።-ዩናይትድ ስቴትስ ፣የሱዳኑን የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበርን አሸባሪ ድርጅት ብላ ለመፈረጅ መወሰኗን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አወደሰች።-የአውሮጳ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን፤ አውሮጳ ከኒውክሌር ኃይል ምንጭ ጥቅም ማፈግፈጓ "ስልታዊ ስህተት" ነበር፤ ሲሉ ተናገሩ።