DW Amharic የየካቲት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
08 March 2026

DW Amharic የየካቲት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን አሰናብቶ አዲስ መሪ መምረጡን አስታወቀ። የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሕመት ማኪ ሳል ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊነት በእጩነት መቅረባቸውን ደገፉ። የኢራን አዲስ መሪ የሚረጠው በሀገሪቱ ሕዝብ እንጂ በዶናልድ ትራምፕ እንደማይሆን የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ተናገሩ። እስራኤል በሊባኖስ ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ባለፈው ሣምንት ብቻ 394 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። ሩሲያ የዩክሬን የጋዝ ማምረቻዎችን ለሁለት ቀናት መደብደቧን የሀገሪቱ የኢነርጂ መሥሪያ ቤት አስታወቀ።