DW Amharic የታኅሳስ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
13 December 2025

DW Amharic የታኅሳስ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ “ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር” ብሪታኒያ እና ቱርክን ጨምሮ አምስት ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ሀገራት “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” የአውሮፓ ኅብረት ጠይቋል። ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችው ውሳኔ እንዳሳዘናት ጅቡቲ አስታወቀች። ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወሰደችው እርምጃ በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት በዋሽንግተን የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት እንደሚጥስ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታወቁ።