zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Toggle Sidebar
zeno
DW
እንወያይ | Deutsche Welle
Politics
Amharic
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Website
Episodes
50
05 April 2026
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ
ጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።
47 min
29 March 2026
በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች
በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህርና የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተመራማሪ ፍቅር ጌታቸው በውይይቱ ተሳትፈዋል።
46 min
22 March 2026
ውይይት፤ ኢትዮጵያ ብርቱ ፈተና የደቀነውን የነዳጅ እጥረት እንዴት ትወጣ?
46 min
22 March 2026
ውይይት፤ ኢትዮጵያ ብርቱ ፈተና የደቀነውን የነዳጅ እጥረት እንዴት ትወጣ?
የኢራን ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የፈጠረው መስተጓጎል ለመቋቋም ሕዝቡ እና ተቋማት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነዳጅ እንዲጠቀሙ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስጠንቅቋል። የነዳጅ ግብይትም መንግስት ባስቀመጠው ታሪፍ መሰረት እንዲከናወን አሳስቧል። ያም ሆኖ ችግሩ ከዓቅም በላይ መሆኑን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው።
46 min
15 March 2026
የኢራን ጦርነት ለዓለምና ለቀጠናችን ያለው አንድምታ
44 min
15 March 2026
እንወያይ፤ የጦርነቱ ዳፋ ወደኛ እንዳይደፋ
ከኢኮኖሚ አንጻር የሖርሙዝ ሠርጥ በዓለም ገበያ ከሚሸጠው የአፈር ማዳበሪያ እስከ 30 በመቶ ወይም 16 ሚሊዮን ቶን የሚጓጓዝበት እንደሆነ ይታወቃል። የአለማችን 20 % የነዳጅ ግብይትም በዚሁ መስመር ይተላለፋል።
44 min
08 March 2026
እንወያይ፤ የነጻ ፕሬስ እና የጋዜጠኞች ፈቃድ መሰረዝ ተጽኖ በኢትዮጵያ
43 min
01 March 2026
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት ልጃለም፤ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ዳምጠው ተሰማን በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዷል።
46 min
22 February 2026
እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው?
ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ሆነዋል።
45 min
15 February 2026
እንወያይ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን?
47 min