
About
የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ የአፍሪቃ፣ የእስያና የአዉሮጳ የባሕር መስመር ሕልቅት ነዉ። በባሕር ከሚተላለፉ የዓለም ሸቀጦች ከ12 ከመቶ በላይ ይመላለስበታል።ከዓለም የኢንተርኔት መስመር 17 ከመቶዉ ተዘርግቶበታል።