በሠላምና ልማት የምሁሩ ሚና፤ለኮንሶ ሁለንተናዊ ዕድገት!" በሚል መሪ ቃል በዞኑ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት የተዘጋጀ የተፅዕኖ ፈጣሪ ምሁራን አንድነት ምክክር መድረክ መወያያ መነሻ ሀሳብ ሰነድ
10 April 2025

በሠላምና ልማት የምሁሩ ሚና፤ለኮንሶ ሁለንተናዊ ዕድገት!" በሚል መሪ ቃል በዞኑ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት የተዘጋጀ የተፅዕኖ ፈጣሪ ምሁራን አንድነት ምክክር መድረክ መወያያ መነሻ ሀሳብ ሰነድ

Konso Digital Radio podcast

About

"በሠላምና ልማት የምሁሩ ሚና፤ለኮንሶ ሁለንተናዊ ዕድገት!" በሚል መሪ ቃል በዞኑ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት የተዘጋጀ የተፅዕኖ ፈጣሪ ምሁራን አንድነት ምክክር መድረክ መካሄድ ጀመረ፣

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም : የምሁራን ምክክር መድረኩ በአንድነት ዙሪያ መልዕክት አዘል የኮንሶ ባህላዊ ኪነት ባንድ ጭፈራ፣በሀገር ሽማግሌዎች ቡራኬ እንዲሁም በኃይማኖት አባቶች ፀሎት ነው የተጀመረው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ፣ የኮንሶ ህዝብ ከ5 መቶ ዓመታት በፊት በራሱ ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ራስን በራስ በማስተዳደር የራሱ የሆነ ሀገር በቀል ዕውቀትና ጥበብ እንዲሁም ድንቅ ባህላዊ ዕሴት ያለው ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል።

የተፈጥሮ የአፈር ጥበቃ የእርከን ስራ፣በሞራ የሚደረገው ባህላዊ እርቅ ስነ ስርዓት፣ የኮንሶ ማህበረሰብ ጥንታዊ ሀገር በቀል ጥበብና ባህላዊ ዕሴቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ያሉት የተከበሩ አቶ ገለቦ፤በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ የኮንሶ ተወላጅ ምሁራን አባቶች ያሻገሩልንን የአብሮነትና አንድነትን በማጽናት አካባቢያችንን ለማሳደግ ጠንክረን መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሠላም ከሌለ ልማት የለም፣ልማት ከሌለ ደግሞ ዕድገትና ለውጥ አይኖርም ያሉት የተከበሩ አቶ ገለቦ፤በዓለም የተመሰከረልንን ባህላዊ ዕሴቶችና ቅርሶቻችንን በመጠበቅና በመንከባከብ የጥንት አባቶች ታሪካችንን ለትውልድ ለማሻገር አጽንኦት ሊንሰጠው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ለውጥ ከራስ ጀምሮ ወደ ሀገር ይሻገራል ያሉት የተከበሩ አቶ ገለቦ፤በምሁራኑ ዘንድ እያበበ የመጣውን አንድነትና አብሮነትን በማጠናከር ሠላምን ማጽናት ለአንድ አካል የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ የውስጥ አንድነታችንን በማጠናከር ለሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የዕለቱ ክብር እንግዳ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ ለአንድ አካባቢ ሠላምና ልማትን ለማረጋገጥ የምሁሩ አንድነት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተሰብስበን ስለ አካባቢያችን ልማትና ሠላም በጋራ እንዲንመክር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ የተሳካ እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመድረኩ ከፌዴራል፣ከክልል፣ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ከዞን እንዲሁም ከወረዳዎች የተወጣጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ምሁራን፣ የሀይማኖት ፎረም ጉባኤ ተወካዮች፣የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳፉ ሲሆን የምክክር መድረኩ ሙሉ መረጃ ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለስበታለን።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም