Skip to content
zeno
Create a Station
Explore
Podcasts
Audiobooks
Bible
By Genre
By Location
By Language
Religious
Music
News
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
Episodes
10
05 October 2026
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏል
ከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም
05 October 2026
የመስከረም 25 ቀን 2019 የስፖርት መሰናዶ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2019 የእግር ኳስ ውድድር ዘመን በተያዘው ሳምንት ይጀመራል። ቡንደስ ሊጋን ጨምሮ ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሊጎችም አርብ እና ቅዳሜ ወደ ውድድር ይመለሳሉ። ሐና ደምሴ ያዘጋጀችው የዛሬው የስፖርት መሰናዶ እነዚህን ጨምሮ አትሊቲክስ እና ሜዳ ቴኒስን የተመለከቱ ዘገባዎች አካቷል።
05 October 2026
በአማራ ክልል የጻግብጅ እና አበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ
በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን አበርገሌ እና ፃግብጂ ወረዳዎች ከወራት በኋላ የመንግሥት መዋቅር በመመለሱ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ቢጀምሩም፣ ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት፣ የሰው ሕይወት መጥፋት ያሳደረው ሀዘን እንዲሁም የረሃብና የደህንነት ስጋት እንደተቀነባቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
05 October 2026
የፌዴራል መንግስት ኃይሎች መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላ የከተማዋ ሁኔታ
በሰሜን ኢትዮጳያ ዳግም ጦርነት ካገረሸ በኋላ ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና አጋሮቹ የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን መቆጣጠራቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንን ተከትሎ በትናንትናው እለት የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ፤ በኢንተርኔት የተደገፈ የባንክ ስርዓት ደግሞ በከፊል መመለሱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
05 October 2026
ዛሬ የተመሠረተው መንግሥት የሚጠብቁት አንገብጋቢ የፀጥታ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ ያቋቋመው መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ተመስርቷል። የተቋቋመው መንግሥት ከውስጥ አንገብጋቢ የፀጥታና የደኅንነት እንዲሁም፣ ከብሔራዊ ጥቅም አንፃር ከጎረቤት ሀገራት ብርቱ ቀጣናዊ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች የሚጠብቁት ነው።
05 October 2026
የአፍሪቃ ቀንድን የተመለከተው የኤርትራ ፣ሶማሊያ ፣ሱዳን እና ግብፅ መሪዎች የጋራ መግለጫ
የግብጽ፤ ሱዳን፤ ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት በግብጽ በኤል አላሜይን የወደብ ክተማ ከተካሄደው የግብጽና አፍሪካ ቢስነስ ጉባኤ ጎን ባካሂዱት የአራትዮሽ ስብሰባ፤ በአፍሪካ ቀንድና የቀይ ባህር ደህንነት ላይ የጋራ መግለጫ አውተዋል።
04 October 2026
አዲስ የሚመሰረተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት ቀዉስ ሊያወጣ የሚችል መፍትሄን ያገኝ ይሆን?
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ፤ አዲስ መንግሥት የሚመሰርተዉ፤ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዲስ ጦርነት ተቀሰቀሰ ከተባለ በኃላ ነዉ። ጦርነቱ የጀመረዉ በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት፤ የአማራ ፋኖ፤ የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ሰራዊትን ጨምሮ 7 አማፂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የጋራ ጥምረት በመሰረቱ በሁለተኛዉ ቀን መሆኑ ነዉ።
03 October 2026
የመብራትና የስልክ መሰረተ ልማቶች በላሊበላ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ተጎድተዉ የነበሩ የመብራትና የስልክ መሰረተ ልማቶች በላሊበላ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ በላሊበላ የነበሩ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን በአየርና በየብስ የማስወጣት ስራዉ ሲቀጥል በደቡብ ወሎ እና አላማጣ አካባቢዎች ደግሞ አዳዲስ ግጭቶችና የሸቀጦች ዋጋ ንረት መከሰታቸው ተመልክቷል።
03 October 2026
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ የኤርትራ አሥር፣ የግብጽ አንድ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ በሰጠች ማግስት የተደረገ ነው
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በዓለም አቀፍ የግንኙነት መርህ ጉልህ የዲፕሎማሲ እርምጃዎች የተስተዋሉበት ሳምንት እያሳለፈ ነው።የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ቀይ ባሕርን፣ የአደንና የአረብ ባህረ-ሰላጤን እንዲሁም የናይል ተፋሰስን ያካተተውን ቀጣና በሚመለከቱ ጉዳዮች ለመወያየት ዛሬ ጥዋይ ካይሮ ገብተዋል።
30 September 2026
በትግራይ የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትግራይ ክልል ቅርንጫፎች የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” የሚል አቋም እንዳላቸው የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል። እርምጃው በትግራይ እና ከክልሉ ውጪ የሚገኙ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል። ይህ የዕለት ተዕለት ወጪዎችን ለመሸፈን ችግር ፈጥሯል።