zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
11
05 April 2026
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ
የዓለም የቱሪዝም፣ የዓየር መንገድና የሆቴል ኩባንዮች ከስረዋል።የከፋዉ ኢራን የሆርሙስ ወሽመጥን መዝጋትዋ ነዉ።የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ ዘይት፣ የማደበሪያ ንጥረ ነገር፣ ማዕድናት፣ የግብርና ዉጤቶችና ሌሎች ሸቀጦች የሚተላለፍበበት መስመር በመዘጋቱ ጦርነቱን የከፈቱት የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤልን ጨምሮ የዓለም ምጣኔ ሐብት እየተሽመደመደ ነዉ።
04 April 2026
የነዳጅ ዘይት እጥረትና አፍሪቃ
ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ አንድ ወር አለፈ። አፍሪቃ ጦርነቱን ተከትሎ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት መስተጓጎል ያስከተለውን የኃይል አቅርቦች ጫና ለመቋቋም እየታገለች ነው።
04 April 2026
የአውሮጳ ሕብረት አዲሱ የሳህል ትብብር እቅድ
የአውሮጳ ሕብረት ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር ያለውን ትስስር በአዲስ መልክ አስተካክሎ ጉድኝነት ለመፍጠር እየሞከረ መሆኑን ይፋ አድርጓል። በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ፤ ቻይና እና ሩሲያ ተጓዳኝነት በሳህል አካባቢ ተመራጭነት እያገኘ መሄዱ የአውሮጳ ሕብረት አቀራረቡን እንዲያጤን ግድ ብሎታል።
04 April 2026
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ለ1,224 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ከማረሚያ ቤትና ተጠሪነቱ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሆነ የይቅርታ ቦርድ የቀረበለትን 1 ሺህ 463 በይቅርታ ልቀቁን ጥያቄን ሲያስተናግድ 239 የሚሆኑትን 'ይቅርታ አይገባችሁም' ሲልም ከልክሏል።
04 April 2026
«ሚልዮኖች ይሳተፉበታል» የተባለው የበይነመረብ ትዕይንተ ሕዝብ
« በኢትዮጵያውያን መካከል አዲስ የእርስበእርስ መተማመን በመፍጠር ለጋራ ችግር በጋራ የመታገልና የማሸነፍ ስሜትን ማጠናከር አንዱ የሰላማዊ ሰልፉ ዓላማ ነው» ብለዋል።
03 April 2026
ጋሪን የተኩት "ባጃጆች" እና ወጣት አገልግሎት ሰጪዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ “ባጃጅ” ተብለው የሚጠሩ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በርካታ ዓመታት ተቆጠሩ። በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተስፋፍተው የሚገኙት ተሽከርካሪዎች በተለይ ለወጣቶች የገቢ ምንጭ ናቸው።
01 April 2026
የኢራን ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል”
በኢትዮጵያ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት በአማካይ በቀን ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ቀንሷል። ሀገሪቱ የኢራን ጦርነት ሲቀሰቀስ የገዛችውን 180,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ማስገባት አልቻለችም። በወር ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ለመደጎም መገደዱን የገለጸው መንግሥት ዜጎች “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክሯል።
31 March 2026
የኢራኑን ጦርነት ተጽእኖ ለመቋቋም የኢትዮጵያ አየርመንገድ እርምጃ
በመካከለኛው ምስራቅ እና ገለፍ አገራት ዙሪያ እያሰጋ ያለው ጦርነት ሁኔታው እየታየ በተወሰነ መልኩ በረራ እየተጀመረባቸው ያሉ አገራትም ስለመኖራቸው አቶ መስፍን በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡
30 March 2026
የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለኢትዮጵያ «በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ»
የቀውሱ ዳፋ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ላይ የማይቋቋሙት እየሆነባቸው ነው ። በዚህ ደግሞ አፍሪቃ እና በማደግ ላይ ያሉ የደቡባዊ እስያ ሃገራት ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸው በግልጽ እየታየ ነው። ሙሉ በሙሉ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት በሚመጣ ነዳጅ ላይ የምትደገፈው ኢትዮጵያም በቀጥታ የዚህ ቀውስ ቀጥተኛ ሰለባ ሆናለች።
29 March 2026
በኢትዮጵያ ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች
በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ የእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? ዶቸ ቨለ አራት እንግዶች በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ አወያይቷል።