የዛሬ ጥያቄዎች
1. ቤተ ክርስትያንን ሊከፍል ሊለያይ የሚመ’ጣ የወንጌል ትምህርት ወደ ቤተ ክርስትያን ሲመጣ የአንድነት እና የህብረት መሰረት ሆነን መቆም የምንችለው እንዴት ነው?
2. ሰው እግዚአብሔርን እያወቀ መከተል የሚችለው እንዴት ነው? ሳያውቅ ከመከተል ኪሳራስ ለመውጣት ምን ማድረግ አለበት?
3. በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን ስለት አውቀን መመለስ የለብንም ወይ?
4. እጊዚአብሔር አብረውን እንዲቆሙ የሰጠንን ሰዎች ማንነታቸውን አካሄዳቸውን ማወቅ አለብን ወይ?
5. በልማድ በምናደርገውና በእምነት በምናደርገው መካከል ያለውን ግንኙነት ብታብራራልን?
6. የምናደርገው ነገር ከእግዚአብሔር ነው እያልን ወደ ብርሃን መምጣት የሚያቅተን ለምንድን ነው?
7. ሁለት ዐይነት ሰዎች አሉ የራሳቸው መንፈሳዊ ትክክል የሚመስላቸውና ሌሎቹ ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ትክክል ነው የሚሉ የሚለውን ብታብራራልን?
8. ካልጠበቅነው ነገር እግዚአብሔር መልስ አለው የሚለው ይብራራልን።
9. የእኛ ነገር የእግዚአብሔርን ግቡኝት እንዲፈጥን ያደርገዋል ወይ?