05 January 2022
ወንጌልና መንግስተ ሰማያት
መልአክና ሰው የተፈጠረው ለአምልኮ ስለሆነ ወንጌልም ወደ ሕይወት ካመጣን በኃላ ወደ አምልኮ ነው የሚያደርሰን፣ በትክክለኛ አምልኮ ከአምላካችን ጋር ስንገናኝ የእግዚአብሔርን ትልቅነት እያየንና እግዚአብሔር በስራው ጻድቅ መሆኑን እየተረዳን በምናልፍበት ሁሉ እርሱን ማመስገን እንጀምራለን፣ መርገማችንን ሽሮ የመንግስቱ ወራሾች ያደረገን አምላካችን እዚህ ምድር ላይ ያስቀመጠን ለመንግስቱ ስራ መሆኑ ሲገባን ዛሬ የምለምናቸው ነገሮች ያንሱብንና በምስጋና እንሞላለን፣ በምስጋና ደግሞ ብዙ ቀንበራችን ይሰበራል ብዙ ድልንም እንቀዳጃለን፣